ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ግብርና ዘርፍ ስር ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪዎች በሻሎ እርሻ ልማት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የቅድመ ወላጅ ዶሮ (Grand Parent) ፕሮጀክት አስመረቀ፡፡
የቅድመ ወላጅ ዶሮ እርባታ ፕሮጀክት ከፍተኛ የእንቁላል እና የስጋ ምርት መስጠት የሚችሉ የዶሮ ዝርያዎችን በመጠቀም ጥራት ያለው የዶሮ ስጋ ምርት እና እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በከፍተኛ መጠን ማምረት የሚያስችል ነው።
ፕሮጀክቱ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ተመርቋል።
በብርሃኑ አበራ (ከሀዋሳ)