በኢትዮጵያ የአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠየቁ

በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ በአገሪቱ ጉዳይ ኤምባሲዎቹ እየተከተሉት ያለውን ያልተገባ አካሄድ በተመለከተ ነው ማብራሪያ የጠየቀው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል በኤምባሲዎቹ በኩል እየወጡ ያሉት የተሳሳቱ መግለጫዎች አግባብነት እንደሌላቸው አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በኤምባሲዎቹም ሆነ በአሜሪካ አስተዳደር ከሚያደርጉት የሽብር መንዛት ተግባር እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የአፍሪካዊያን ጉዳይ በአፍሪካዊያን እንዲፈታ ለእኛው ተውልን ሲል ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ለአገራቱ አምባሳደሮችና ኤምባሲዎች ደብዳቤ ጽፏል።