በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ አገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናት ሊካሄድ ነው

ሚያዝያ 05/2013 (ዋልታ) – በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ አገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናት ሊካሄድ ነው።

ጥናቱ እድሚያቸው ከ16 አመት በላይ የሆኑ 13 ሺህ 600 የማህበረስብ ክፍሎችን ያካትታል ተብሏል።

በየጊዜው እየተዛመተ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተህዋሲ ሥርጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በተደጋጋሚ እየተነገረ ሲሆን፣ በስርጭቱ ላይ ሳይንሳዊ የመከላከል ስራ ለመስራት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ከሚያዚያ 7 ጀምሮ ለአንድ ወር በሚቆየው ጥናቱ 160 ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዳሰሳ ጥናቱ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ሳሮ አብደላ የጥናቱ ግኝት ለሚተገበረው የኮቪድ-19 የመከላከል ስራ በግብአትነት እንደሚውል ገልፀዋል።

ከሁለት ቀናት በኋላ የሚጀምረው ጥናትም የተሳካ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ የመንግስት አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

(በደምሰው በነበሩ)