በኢትዮጵያ 1949 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

መጋቢት 16/2013 (ዋልታ) – ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 423 የላቦራቶሪ ምርመራ በኢትዮጵያ 1949 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 194 ሺህ 524 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 530 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151 ሺህ 172 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 741 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 40 ሺህ 609 ሰዎች መካከል 744 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ2 ሚሊዮን 308 ሺህ 568 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።