በኢትጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን

ኅዳር 10/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ወደ አዲስ አበባ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም ሆነ በየትኛውም የኢትጵያ አየር ክልል ላይ የሚደረግ በረራ ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከስጋት ነጻ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ስጋት እንዳለበት ተደርጎ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረተ ቢስና ከዕውነታው የሚቃረን መሆኑንም አመላክቷል፡፡

የአገሪቷ የአየር ክልል እና አየር መንገዱ ፍጹም ደህንነቱ የተጠበቀ ለመሆኑ ለተጠቃሚዎቻችን እናረጋግጣለንም ብሏል።

ዓለም አቀፍ የጥንቃቄ እና ደህንነት ደረጃ መስፈርት በሚያዘው መሰረትም የተጠቃሚዎቻችን ምቾትና ደህንነት ተጠብቆ ከሥጋት ነጻ የሆነ በረራ እንዲያደርጉ የጥንቃቄ መስፈርቶችን እንደወትሮው ሁሉ እንደሚተገብር ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።