በኢኮኖሚው ግንባር በሚካሔደው ፍልሚያ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አሸናፊ መሆን እንደሚገባ ተገለፀ

ታኅሣሥ 5/2014 (ዋልታ) በኢኮኖሚው ግንባር በሚካሔደው ፍልሚያ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አሸናፊ መሆን እንደሚገባ ተገለፀ።

በዚህም የሀገር ኅልውና ማስጠበቅ ላይ ሁሉም መረባረብ ይገባል ተብሏል።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት “የከይዘን ፍልስፍና ትግበራዊ ለሀገራዊ ጥራትና መሻሻል” በሚል መሪ ሀሳብ ለ7ኛ ጊዜ በሚደረገው የከይዘን ሽልማትና እውቅና ላይ ነው።

የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ ሽሰማ ገ/ስላሴ ሀገር ከገጠማት ችግር እንፃር በኢኮኖሚው  በሚደረገው ጦርነት የከይዘን ፍልስፍና ሀብትን በውጤታማነት መጠቀም የሚያስችል በመሆኑ  የድርጅቶችን ቁልፍ ችግሮች በመለየት ሀገርን የሚያሳድግ አስተዳደሮችን ማፍለቅ ይገባል ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አስናቀ ጉደሴ በበኩላቸው በካይዘን ፍልስፍና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የማስረፅ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በ2013 ዓ.ም በከይዘን ትግበራ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማትና ቡድኖች የከይዘን ሽልማት እውቅና እንደሚሰጥ ታውቋል።

በዙፋን አምባቸው