በኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ በወልዲያና አካባቢ ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ

ጥር 20/2014 (ዋልታ) በ66 ኪሎ ቮልት ኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ወልዲያ፣ መርሳ፣ ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ከደሴ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ወልዲያ ማከፋፋያ ጣቢያ በተዘረጋው መስመር ላይ ሀብሩ ወረዳ ቀርጨም በር ቀበሌ አካባቢ በባለ አራት ቋሚ ምሰሶ ላይ ባልታወቀ ምክንያት በደረሰ የእሳት አደጋ ምሶሶዎቹ ሙሉ በሙሉ በመቃጠላቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧልም ነው የተባለው፡፡
ምሶሶዎችን በመተካት አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ ሕዝቡ በትእግሥት እንዲጠብቅ ጠይቋል።