በኤሜሬት ዓለም ዐቀፍ ቀይ ጨረቃ ማኅበር የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል በሮቤ ከተማ በአረብ ኤሜሬት ዓለም ዐቀፍ ቀይ ጨረቃ ማኅበር ድጋፍ ከ147 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው፡፡

ከፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የመዳ ወላቡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን 24 ክፍል እና ከ 2 ሺሕ 400 በላይ ተማሪዎችን የማስተማር አቅም አለው።

ግንባታው በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቆ በተያዘው የትምህርት ዘመን ከአንድ ሺሕ በላይ ተማሪዎችን እያስተናገደ ይገኛል።

የትምህርት ቤቱ በከተማዋ እና አካባቢው ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተነግሯል።

ሚልኪያስ አዱኛ (ከሮቤ)