በእንግሊዝ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ከ10 ሺሕ ፓውንድ በላይ ድጋፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 10/2014 (ዋልታ) በእንግሊዝ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች አሸባሪው ሕወሓት በከፈተው የእብሪት ወረራና ጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሺሕ ፓውንድ በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉ በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የሚውል መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በዓለም ዙሪያ ያሉ የኢትዮጵያና ወዳጆቿ የዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በቀረበው አገራዊ ጥሪ መሰረት ለአገራዊ ሉአላዊነት መጠበቅ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙና ድጋፋቸውን እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡