በእውነተኛ ሀገራዊ ታሪክ ላይ የተመሰረተው “ንስሮቹ” የተሰኘው ፊልም ተመረቀ

ግንቦት 8/2015 (ዋልታ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተዘጋጀውና በታምራት መኮንን ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራው “ንስሮቹ”  (THE EAGLES) የተሰኘው ፊልም ተመረቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተዘጋጀውንና  በታምራት መኮንን ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራው “ንስሮቹ” የተሰኘው ፊልም መርቀው ለእይታ ይፋ አድርገዋል።

በፊልሙ የምረቃ መረሀ ግብሩ ወቅት ንግግር ያደረጉት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ፤ ያደጉ ሀገራት የብሔራዊ ደህንነት ተቋማት አሁን የደረሱበትን አቅም የገነቡት የኪነ ጥበብን አይተኬ ሚና ተጠቅመው መሆኑን ጠቅሰው፤ ከአንድ አመት በፊት ኢትዮጵያ ካሳለፈችው ታሪክ  መካከል አንድ ሰበዝ በመምዘዝ “ንስሮቹ” የተሰኘውን ፊልም ለመስራት መቻሉን ገልፀዋል።

ታሪኮቻችን ከሪፓርት ማለፍ መቻል አለባቸው ያሉት ዳሬይክተር ጀነራሉ፤ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የሀገራችሁን ታሪክ ወደ ፊልም፤ መጽሐፍና ሌሎች የኪነ ጥበብ ዘውጎችን እንዲቀይሯቸው በመጠየቅ ተቋማቸውም በቀጣይ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ፊልሙን ለማጠናቀቅ ከአንድ አመት በላይ ጊዜ መውሰዱም በወቅቱ ተነግሯል።

በደረሰ አማረ