በኦሮሚያ በአንድ ጀምበር 4 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 11/2014 (ዋልታ) “አሻራችን ለትውልዳችን ፣ ለትውልድ እንስራ ፣ ኦሮሚያያን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር 4 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርኃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

መርኃ ግብሩን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጆጎ ጉዴዶ ቀበሌ ተገኝተው አስጀምረዋል።

በ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እንደ ኦሮሚያ ክልል 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።

በዚህም በምሥራቅ ሸዋ ዞን 25 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርኃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በአሳንቲ ሀሰን