በኦሮሚያ ክልል ለጤና ባለሙያዎች እውቅና የመስጠት ስነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው

ለጤና ባለሙያዎች እውቅና መስጠት

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ግንባር ቀደም ሚና ለተጫወቱ የጤና ባለሙያዎች እውቅና የመስጠት ስነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው።

በስነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ የኮሮና ቫይረስ መደ ኢትዮጵያ በገባበት ወቅት የጤናው ሴክተር ሰራተኞት አስፈሪውን ጊዜ በመጋፈጥ  ያደረጉት ተጋድሎ በታሪክ የሚጠቀስ አኩሪ ገድል ነው ብለዋል።

የጤና ባለሙያ በመሆኔ ቤት መቆየት አልችልም በሚል መፈክር ባለሙያዎቹ በሰሩት ስራ ህዝባቸውን ከወረርሽኙ መታደግ መቻላቸውን ገልጸዋል።

ባለሙያዎቹ በአንድ እጃቸው የኮሮና ቫይረስን በሌላው እጃቸው መደበኛ የጤና ስራዎችን በመስራተወ በአጠቃላይ የክልሉ የጤና ዘርፍም ከወትሮው የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ አድርገዋል ብለዋል።

የዛሬው ፕሮግራም በአንድ ወገን የምስጋና በሌላ ወገን ለሁለተኛ ተልዕኮ የምንዘጋጅበት ግዜ ነው ያሉት ዶ/ር መንግስቱ፣ ዴልታ የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ በመሆኑ የጤናው ሴክተር ሰራተኞች ሶስተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሪቱ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የተለመደውን ተጋድሏቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ባለሙያዎቹ የገቡትን የሙያ ቃለመሃላ በመተግበር የቫይረሱ ሥርጭት በክልሉ እንዳይስፋፋ የጎላ አስተዋፅኦ እንደነበራቸውም ተገልጿል።

(በአሳየናቸው ክፍሌ)