ጥቅምት 20/2014 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ361 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለፀ።
ቢሮው ከ21 ዞኖችና ከ19 የክልሉ ከተሞች ከተውጣጡ የዘርፉ ሴክተሮች ጋር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ 100 ቀናት እቅድ ላይ በአዳማ መክሯል።
የቢሮው ኃላፊ አህመድ እንዲሪስ ለኢዜአ እንደገለጹት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ361 ሺሕ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።