በኦሮሚያ ክልል በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት የመስጠት መርኃግብር እየተካሄደ ነው

ግንቦት 04/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል በ2012 የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት የመስጠት መርኃግብር እየተካሄደ ነው።

በሽልማት ሥነሥርዓት ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዳሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዛሬው መርሃግብር 152 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ይበረከትላቸዋል ነው የተባለው።

የክልሉ መንግስት በዘንድሮው ዓመት ለትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ በኢፋ ቦሩ ፕሮጄክት ከ5 ቢሊየን ብር በላይ በመመደብ 147 ትምህርት ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ እያስገነባ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

(በአሳየናቸው ክፍሌ)