ሰኔ 29/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልል መንግስት በ2013 ዓ.ም በግብርና ምርቶች ላይ የ2 ነጥብ 3 በመቶ የምርት ጭማሪ ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡
ስምንት ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኦሮሚያ ክልል የ2013 ዓ.ም የግብርና ስራ አፈፃፀም ግምገማ በመካሔድ ላይ ይገኛል።
የኦሮሚያ ክልል እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ ዳባ ደበሌ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥን ጨምሮ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት እና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በመጠን እና በአይነት የማሳደግ ስራ በተያዘው አመት ክልሉ በስኬት የሠራቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።
በክልሉ በተያዘው አመት የግብርናው ስራ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ የዘርፋ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ተመላክቷል።
(በድልአብ ለማ)