ሐምሌ 21/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል በ2013 በጀት እመት የስራ አፈፃፀም እንዲሁም የቀጣይ በጀት አመት የስራ አቅጣጫ ከክልሉ በተውጣጡ የስራ አመራሮች ውይይት ተካሂዷል፡፡
ለሶስት ቅናት በተደረገው የግምገማ እና ውይይት መድረክም በዋናነት በክልሉ የተሰሩ የልማት ስራዎች ምን ያህል ውጤታማ ናቸው እንዲሁም ምን ያህልስ ማህበረስብ ተኮር ስራዎች ተከውነዋል በሚል መነሻ ውይይት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በቀጣይም ማሻሻያ የሚሽቱ ክፍተቶችን በምን መልኩ መስተካከል እንዳለባቸው ክልሉ መክሯል፡፡
በ2013 በጀት አመትም በክልሉ በተሰሩ የልማት ስራዎችም አመርቂ ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
በክልሉም የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዞኖች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡
በክልሉም እንደ ሀገር የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከግብ ከማድረስ አኳያ በችግኝ ተከላ በንቃት መሳተፉን ተከትሎ የካርበን ልቀት በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራ መመዝገቡም እንዲሁ ተገልጿል፡፡
(በሄብሮን ዋልታው)