ሚያዝያ 18/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል የመንግስት እና የፓርቲ የሶስተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን፣ በመስኖ ልማት ስራ እየለሙ የሚገኙ ስንዴ፣ አቮካዶ እና የማር ምርትን እንደምሳሌ አንስተዋል፡፡
የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህልም እያደገ መምጣቱን በመድረኩ መግለፃቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/%D8%AA%D9%84%D9%81%D8%B2%D9%8A%D9%88%D9%86-%D9%88%D8%A7%D9%84%D8%AA%D8%A7-%D8%A8%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B1%D8%A8%D9%8A-Walta-TV-Arabic-102134881551994/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!