ታኅሣሥ 12/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል እርሻና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አዘጋጅነት በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ከሚገኙት ከተፋሰስ ልማት ሥራዎች ተሞክሮ ለመውሰድ እየተደረገ ያለው ጉብኝት ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው፡፡
በዚህም ከተለያዩ የክልሉ ዞኖች ተሞክሮውን ለመውሰድ የመጡ እንግዶች በምዕራብ ሀረርጌ ዶባ ወረዳ የሚገኘውን ወልታኔ የተፋሰስ ልማት ሥራ ጎብኝተዋል።
በዶባ ወራዳ 24ሺሕ 628 ሄክታር መሬት ተከልሎ እየለማ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ቀደም ይህ መሬት ደረቅና ያልለማ እንደነበረ ተገልጿል።
አሁን ላይ ግን የአከባቢው ነዋሪ በነቂስ ወተው በተፋሰስ ሥራ በማልማታቸው ድርቀቱ ቀርቶ ለምለም መሆኑንም የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከተፋሰስ ልማት ሥራዎች ተሞክሮን ለመውስድ ከተለያዩ ዞኖች የመጡ እንግዶች በበኩላቸው በዞኑ እየተሰራ ያለውን የተፋሰስ ልማት ሥራን በማድነቅ ከዚህ ያገኙትን ተሞክሮ ወደ አከባቢያቸው ሲመለሱ ሥራ ላይ እንደሚያውሉ ገልፀዋል፡፡
በታምራት ደለሊ