በኦሮሚያ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ነሃሴ 13/2013 (ዋልታ) – የግብርናውን ዘርፍ ከትራከተራይዜሽን ወደ መካናይዜሽን ለማሸጋገር የሚያስችሉ ስራዎች እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የኦሮሚየ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ መንግስት ዘርፉን ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት ጆን ዲር ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በመሆን ለአርሶ አደሩ እያቀረበ ከሚገኘው ትራክተሮች እና ኮምባይነሮች በተጨማሪ ለተለያየ የእርሻ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን ይፋ አድርጓል።

እነዚህም ማሽኖች ጤፍን በመስመር ከማረስ ጀምሮ የተለያዩ ዘር መዝራት እና ችግኞችን መትከል የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

(በሚልኪያስ አዱኛ)