በኦሮሚያ ክልል 6ሺህ 111 የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ለአርሶአደሮች ተከፋፈለ


ሐምሌ 08/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል የመስኖ ልማት ይበልጥ ለማሳደግ 6 ሺህ 111 የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ለአርሶአደሮች ማከፋፈሉ ተገለጸ።
የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹን የክልሉ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ከውጭ ያስመጣቸው ሲሆን፣ በመስኖ ልማት ላይ ለተሰማሩ
አርሶአደሮች እና ማህበራት ነው የተከፋፈለው፡፡
እያንዳንዱ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ አምስት ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ የክልሉን መስኖ ልማት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ታምኖበታል።
(በአሳየናቸው ክፍሌ)