በክልሉ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል

ሚያዝያ 23/2014 (ዋልታ) በሐረሪ ክልል የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ሕዝበ ሙስሊሙ 1ሺሕ 443ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያከብር ፖሊስ በክልሉ ከሚገኙ የተለያዩ የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግብረ ኃይል አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን አመልክተዋል።

ምዕመናኑ ሶላት ወደሚያደርጉበት ስፍራ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ዋና ዋና መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑና አማራጭ መንገዶች ደግሞ ለተሽከርካሪ ክፍት እንደሚደረጉም አንስተዋል፡፡

ሆኖም በክልሉ አንድ አንድ ሰላም የማይፈልጉና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ግጭት ለማስነሳት የሚንቀሳቀሱ አካላት እንዳሉ የጠቆሙት ኮሚሽነር ነስሪ ይህ ዓይነት ድርጊት ሲያጋጥም ህብረተሰቡ ማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር እያከናወነ የሚገኘውን ሰላም የማስከበር ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል  መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።