በክሪፕቶ ከረንሲ ክፍያ ከመፈጸም ኅብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

ግንቦት 29/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ በክሪፕቶ ከረንሲ ክፍያ መፈጸም በብሔራዊ ባንክ እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ ኅብረተሰቡ ከሕገ ወጥ ተግባር ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለዋልታ በላከው መረጃ በአሁኑ ወቅት ከሕግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ እንደ ቢትኮይንና የመሳሰሉት የምናባዊ ንብረት ወይም ገንዘብ አገልግሎት በሀገሪቱ እየተስፋፋ መምጣቱን በጥናት ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡

ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንኩ እውቅና ወጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታዎች እየፈጠረ እንደሆነም ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጾ ኅብረተሰቡም ይህንን ሕገ ወጥ ተግባር የሚሰሩ አካላትን ሲመለከት ለብሔራዊ ባንክና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW