በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – “በጎ ፈቃደኝነት ለመደጋገፍና ለመግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀምሯል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ሙቀት ታረቀኝ በክረምቱ ወራት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤት እድሳት አገልግሎት ጨምሮ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።

በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞች የበጎ ፈቃድ እንደሚሰጡም ተጠቁሟል።

(በሱራፌል መንግስቴ)