በኮሎራዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ

ነሐሴ 30/2013 (ዋልታ) ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ኮሎራዶ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 100 ሺሕ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ገንዘቡን ካዘጋጇቸው ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
ገንዘቡንም ለዚሁ ዓላማ እንዲውል በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ግድቡ ተጠናቆ ወደ ሥራ እስኪገባ ድረስም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡