በወላይታ ሶዶ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ተጀመረ

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወላይታ ሶዶ ከተማ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ተግባር አስጀመሩ።

በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ይሁን አሰፋ እና የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ማሄ ቦዳ እንዲሁም የወላይታ ዞን አመራሮች በተገኙበት ተግባሩ ተጀምሯል።

አመራሮቹ በአንዲት እናት ቤት በመገኘት ሥራውን ያስጀመሩ ሲሆን የግንባታ ግብኣቶችንም ማስረከባቸውን የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

ሁሉም ወገን እርስ በእርስ የመተጋገዝና የመተሳሰብ በጎ ተግባርን አዳብሮ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቹን ሊረዳ እንደሚገባም አሳስበዋል።