በወረዳው በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 120 ሽጉጥ ተያዘ

ሚያዝያ 6/2014 (ዋልታ) ቦረና ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 1 ሚሊየን 80 ሺሕ ብር የሚያወጣ 120 ፋልኮል ሽጉጥ መያዙን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ምክትል ኢንስፔክተር ኡስማን ሰይድ ከብሔረዊ መረጀና ደኅንነት በደረሰ ጥቆማ መሠረት መነሻውን ከሰሜን ጎንደር ያደረገ አንድ ኮብራ መኪና 120 ፋልኮል ሽጉጦችን ጭኖ ወደ ኮምቦልቻ ሲጓዝ በቦረና ወረዳ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ መያዙን ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።