በወረዳው በእሳት ቃጠሎ ንብረት ለወደመባቸው ድጋፍ ለማቅረብ እየተሰራ ነው

ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ) በአፋር ክልል ሃሪ-ረሱ ዞን ሰሙሮቢ ገለአሎ ወረዳ ኩማሜ ከተማ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች መጠለያ ቦታ የማዘጋጀትና ሰብኣዊ ድጋፍ የማቅረብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ወረዳው አስታወቀ።

በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳዳደር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በአደጋው 80 ሱቆችን ጨምሮ 175 ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ሲያወድም በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን የወረዳው ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ሳጂን አደም ገባጌዴ ለኢዜአ ገልጸዋል።

አደጋው በተከሰተበት አካባቢ የነበሩ የቤንዚንና ሌላም ነዳጅ መሸጫ ቤቶች መኖራቸው ለቃጠሎው መባባስ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል።