በወራቤ ከተማ የደረሰው የእሳት አደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ

መስከረም 30/2014 (ዋልታ) በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ በደረሰ የእሳት አደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።
በእሳት አደጋው አራት የላሜራ ቤቶች ተቃጥለዋል።
የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን አብዱረሂም ሁሴን እንደገለጹት፣ የእሳት አደጋው በአንድ ሰው ላይ ጉዳት አድርሷል። ተጎጂውም ህክምና እየተደረገለት መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማው የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የእሳት ቃጠሎው በከተማው የእሳት አደጋ ተሽከርካሪና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል። የደረሰው የአደጋ መጠን በመጣራት ላይ መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!