በወንዶች 3 ሺሕ ሜትር መሰናክል እና በሴቶች 1 ሺሕ 500 ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያ ሁለት የብር ሜዳሊያ አገኘች

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 3 ሺሕ ሜትር መሰናክል እና በሴቶች 1 ሺሕ 500 ሜትር ፍፃሜ ኢትዮጵያ ሁለት የብር ሜዳሊያ አገኘች፡፡

በሴቶች በ1 ሺሕ 500 ሜትር ፍፃሜ በጉዳፍ ፀጋይ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የብር ሜዳሊያ ስታገኝ በውድድሩ ኬንያ የወርቅ እና ብሪታኒያ የነሃስ ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል።

በለመሳሳይ በወንዶች 3 ሺሕ ሜትር መሰናክል ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ማስገኘት ችሏል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ ርቀቱን በሁለተኛነት ለመጨረስ 8፡26.01 ወስዶበታል።

በውድድሩ የሞሮኮ አትሌት ሶፊያን ኤልባካሊ የወርቅ ሜዳሊያን እንዲሁም የኬንያ አትሌት የነሃስ ሜዳሊያ ሲያገኙ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጌትነት ዋለ እና ኃይለማሪያም አማረ 4ኛ እና 10ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስካሁን ሦስት የወርቅ እና ሦስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት በደረጃ ሰንጠረዡ ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!