በወንጭ ሀይቅ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ

ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – “ኑ ኦሮሚያን እናልብስ” በሚል መሪ ሀሳብ በገበታ ለሃገር ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በወንጭ ሀይቅ የችግኝ ተከላ ተካሄደ።

የወንጭና ደንዲ ሀይቆች ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶክተር አብርሃም በላይ በሀገር ደረጃ በሚካሄደው የኢኮ-ቱሪዝም እንቅስቃሴ ውስጥ የወንጪ ደንዲ  ሀይቅ ላይ የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፍ አካባቢው ባለው የተፈጥሮ ሃብት ተጨማሪ ውበትና የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፍ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ በአንድ ቀን ክብረ ወሰን በሆነ የ351 ሚሊየን የችግኝ ተከላ በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ በተመሳሳይ ጊዜ እየተተከለ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ መገርሳ ድርብሳ ተናግረዋል።

ሶስተኛ ዓመቱን በያዘው የአረንጓዴ አሻራ በደቡብ ምእራብ  ሸዋ ዞን 181 ሚሊየን ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን ዛሬ በዞኑ እየተተከለ ካለው 13 ነጥብ 8  ውጭ በክረምቱ  76 ሚሊየን ችግኝ መተከሉ ተገልጿል።

በወንጭ ሀይቅ በዛሬው እለት 10 ሺህ የቅርቀሃ፣ የወይራና ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል።

(በምንይሉ ደስይበለው)