በዞኖቹ እየተስፋፋ በሚገኘው የጉሮሮ ካንሰር መከላከልና ማከም ላይ ምክክር ተደረገ

የካቲት 4/2015 (ዋልታ) በአርሲና ባሌ ዞኖች ከሌሎች ቦታዎች በተለየ እየተስፋፋ በሚገኘው የጉሮሮ ካንሰር መከላከልና ማከም ላይ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ምክክር ተደረገ።

በምክክር መድረኩ የአርሲ ዩኒቨርስቲ፣ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሜዲካል ኮሌጅና አርሲ ነጌሌ ሆስፒታልና ሚዲካል ኮሌጅ አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል።

እስከ አሁን በካንሰር አይነቶችና ስርጭቶች ዙሪያ በተደረጉ ጥናቶች መሰረት የጉሮሮ ካንሰር ከበሽታ አይነቶችና ስርጭቱ እንደ አገር በባሌና አርሲ እንደሚበዛ ታዉቋል።

ይህንን ችግር መለየት፣ መመርመርና ማከም ግዴታ ከመሆኑም በላይ የችግሩ አሳሳቢነት የጎላ በመሆኑ በዛሬዉ እለት መፍትሔን ለማበጀት ምክክር ተደርጓል።

በምክክሩ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ቦኮና ይህ ምክክር ለችግሩ ፍቱን መፍትሄ ለማምጣት የጎላ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የጉሮሮ ካንሰር በሽታን ለመመርመርና ለማከም የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ከመሰል በሙያ መስኩ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር በመስራት የህዝቡን ችግር ለመቅረፍ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዱጉማ አዱኛ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የጉሮሮ ካንሰር ጉዳቱ የከፋ ከመሆኑ የተነሳ ተቋማቶቹ በዚህ ችግር የተነሳ ጉዳት እንዳያጋጥም ሊሰሩ የተስማሙ ሲሆን የመደወላቡ ዩኒቨርስቲም ይህን በሽታ ለመከላከልና ለመመርመር ከመሰሎቹ ጋር በመስራት የህብረተሰቡን ችግር በመቅረፍ የመፍትሄ አካል ለመሆን ዝግጁ መሆኑን የመደወላቡ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት አሕመድ ከሊል (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የጉሮሮ ካንሰር እንደ አገር በባሌና አርሲ ዞኖች ከሰባ በመቶ ተሰራጭቷልም ነው የተባለው።

ዱጋሳ ፉፋ (ከአርሲ)