በደቡብ ክልል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርኃግብር እየተካሄደ ነው

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ይፋዊ የዘር ማስጀመሪያ መርኃግብር በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ እየተካሄደ ነው።

በ2014 የምርት ዘመን በክልል ደረጃ በሚከናወነው የበጋ የስንዴ ዘር ልማት 15 ሺሕ ሄክታር መሬት እንደሚሸፍን ተገልጿል።

በማስጀመሪያ መርኃግብሩ ላይ በርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር፣ በግብርና ሚኒስቴር የፌዴራል የእርሻ ዘርፍ ጀነራል ዳይሬክተር ገርማሜ ጋሩማ፣ የክልል እና የዞን አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችና አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

እንደ ክልል ለሚጀመረው የበጋ ስንዴ ዘር የመዝራት ሂደት የክልልና የዞን አመራሮች በተዘጋጀው እርሻ ላይ በይፋ እንደሚያስጀምሩ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።