በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ነዋሪዎች ድምፅ እየሰጡ ነው

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – ከደሴ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኩታበር ወረዳ ነዋሪዎች ማለዳ 12:00 ጀምረው ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በወረዳ ከተማዋ ከ72 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 6 የፖለቲካ ፓርቲዋች ይወዳደራሉ ነው የተባለው።

በኩታበር-ለ  እና በበሽሎ-ለ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተን ያነጋገርናቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ምርጫው ያለ ምንም ተፅእኖ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

(በቁምነገር አህመድ)