በዱከም የከተማ ግብርና ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተካሄደ

ሐምሌ 9/2014 (ዋልታ) በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አብዱልሃኪም ሙሉ
በዱከም የከተማ ግብርና ኢኒሼቲቭ መርኃ ግብርን አስጀምረዋል።
በዱከም ከተማ እየተሰራ ያለው የከተማ ግብርና የከማዋን ነዋሪ አለፎም የክልሉን እንዲሁም የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጸው የክልሉ መንግሥት የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማዋ የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለፁት የዱከም ከተማ ከንቲባ አብዱልጀሊል አብዱሮ ይህም በትመህርት ቤት፣ በሀይማኖት ተቋማት እና በመንግሥት ቦታዎች ላይ እየተሰራ መሆኑን ገለፀዋል።
በከተማው በግብርና ስራዎች የዶሮ እርባታ፣ የጓሮ አትክልት፣ የከብት እርባታ ይገኙበታል።
ፌናን ንጉስ (ከዱከም)