በዳንሻ ከተማ የአሸባሪውን ሕወሃት ግፍ የሚያወግዝና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 06/2013 (ዋልታ) – በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አስተዳደር በዳንሻ ከተማ የአሸባሪውን ሕወሃት ግፍ የሚያወግዝና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሑመራ ከተማ የተጀመረው ሰልፍም ዛሬ በዳንሻ ከተማ የቀጠለ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ግፍ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሰልፍ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ አሚኮ ዘገቧል፡፡
በአሸባሪው ሕወሃት የሥልጣን ዘመን የደረሰውን ግፍ የሚያወግዙና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወሙ ሰልፎችም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ የተለያዩ ከተሞች ሲደረጉ መቆየታቸው ይታወሳል።