መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዳካር እና በርሊን በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ የቻለ ውጤታማ ሥራ መሰራቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሴኔጋል ዳካር 9ኛው የዓለም ውሃ ፎረም እንዲሁም በበርሊን 8ኛው የኢነርጂ ሽግግር ፎረም ላይ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ ልዑክ ተሳትፏል።
በፎረሞቹ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ የቻለ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራ መሰራቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በኢነርጂው ዘርፍ የማልማት ፍላጎትም አቅምም እንዳላት በመግለፅም በኃይል ልማት ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ኢንቨስተሮች ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ ተችሏል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እያካሄደች የምትገኘው ከብክለት የፀዳ አረንጓዴ ልማት ተሞክሮዋም ቀርቦ እውቅና እንደተገኘበት አንስተዋል።
ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵያ ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም አቋሟንና አፍሪካን በኃይል ለማስተሳሰር እያደረገች የምትገኘውን እንቅስቃሴ በተገቢው መልኩ ማስረዳት መቻሉንም ገልጸዋል።
በትዕግሥት ዘላለም
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW