በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ የሚኖሩ ተሰናባች ሰራዊቶች ለዳግም ዘመቻ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

ነሀሴ 14/2013- የዳውሮ ዞን ነዋሪች በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ያደረጉና ለሀገር ክብር አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል በክብር የተሰናበቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊቶች አሁን በሀገር ላይ የተደቀነውን የአሸባሪውን የህዋሃት ሴራ ለመመከት ለዳግም ዘመቻ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ለሀገር ሰላም ዳግም እስከ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁ ሻምበል ባሻ ምህረት አሰፋ የሀገር ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የአከባቢውን ልማትና ውቤት ማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም በትከረት መስራት አለበት ብለዋል።

የአከባቢያችንና የሀገራችንን ሰላም ለማድፍረስ የሚቃጣውን የትኛውንም ሀይል መቃወማቸውን በመግለፅ ከመንግስትና ከፖሊስ አባላት ጋር በመቀናጀት ለሀገርና ለአከባቢ ሰላም ቀንና ማታ እንሰራለን ያሉት ሀምሳ አለቃ አብዮት መንገሻ ናቸው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አየር ወለድ አሰልጣኝ የሆኑት ፲/አለቃ ታደሰ ጮራሞ በበኩላቸው ኢትዮጵያን ለማዳን መንግስት ላስተላለፈው ጥሪ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው ለሀገርና ለአከባቢ ሰላም ለሎች ተመላሽ ሰራዊቶችን በማደራጀት ወደ ተግባር መገባቱንም ተናግረዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊትንት ከ25 ዓመት በላይ በማገልገል በጉዳት የተሰናበቱ ሻምበል ታረቀኝ አዳሬ ከሀገር ሰላም የሚበልጥ ምንም ነገር ልኖር ስለማይችልና ከመንግስት ጋር የነበረን የሰላም ውል ስላልተቋረጥ ፀጥታን የማስከበሩን ስራ አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

ሻምበል ታረቀኝ አክለውም የአሸባሪውን የህወሓት ተልዕኮ በመቀበልና ለግል ጥቅማችው በየአከባቢው የጥፋት አጀንታ የሚያቀነቀኑት በመለየትን ጥብቅ ክትትል በማድረግ ለህግ እንዲቀርቡ በትኩረት መሰራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በከተማው የሚኖሩና ለዳግም ሀገራዊ ጥሪ ዝግጁ የሆኑ በክብር ተሰናባች ሰራዊቶች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ለመግለፅ የከተማውን ውበት ለማስጠበቅ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።