ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) በዶሮ እርባታ የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የስኬት ጉዞ ማሳያ ነው ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለፁ።
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ግብርና ዘርፍ ስር ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪስ በሻሎ እርሻ ልማት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የቅድመ ወላጅ ዶሮ (Grand Parent) ፕሮጀክት አስመርቋል ።
የግብርና ሚኒስትሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ሜድሮክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክተን በማሳካቱ አመስግነዋል።
በአጭር ጊዜ እቅዶችን ማሳካት መቻላችን በቀጣይ በሚተገበሩ ስራዎች ላይም እንደማያቆሙን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ አመራር እና ህዝቡ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ የግል ዘርፉም ሚናው የጎላ እንደሆነ ሚኒስትሩ አንስተዋል ።
ሀገሪቱ የነበራትን የልመና ታሪክ ለመቀየር በከፍተኛ ቁጭት የተጀመረው የስንዴ ኢኒሼቲቭ አመርቂ ውጤት እያስገኘ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ አስር ከፍተኛ የስንዴ ላኪ ሀገራት ውስጥ መካተት ችላለች ነው ያሉት።
በብርሃኑ አበራ እና ቤዛዊት አበበ (ከሀዋሳ)