በጁባ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ4 ሺህ ዶላር ቦንድ ገዙ

በጁባ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) – በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የአራት ሺህ ዶላር ቦንድ ገዙ።

ጁባ በሚገኘው ደምበሽ ሆቴል የሚሰሩት ኢትዮጵያውያኑ የአራት ሺህ ዶላር ቦንዱን ከመግዛታቸውም በላይ ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ አቅማቸው በሚፈቅደው ሁሉ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ አምባሳደር ነቢል ማህዲ የቦንድ ሰርቲፊኬቶቹን ለሠራተኞቹ ሲያስረክቡ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያውያን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አሻራቸውን ለማኖር በቦንድ ግዢ ላበረከቱት አስተዋፆኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አክለውም የሆቴሉ ባለቤት አቶ አይሸሽም ተካ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ብቻ ሳይሆን በሀገራዊ ልማት ላይ በተለያዩ ጊዜያት እያበረከቱት ያለው አስተጽጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኤምባሲውም ድርጅቱን ለመደገፍ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ መግለጹን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡