በጅማ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ መዝጊያ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 09/2013 (ዋልታ) – በጅማ ከተማ ስታዲየም የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ መዝጊያ መርኃግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የፓርቲው ደጋፊዎች አንድነታችን የማይበጠስ ፣ ሉአላዊነታችን የማይገረሰስ ነው፤ አንድነታችን ብዙሀነታችንን አያጠፋውም ብዙሀነታችን አንድነታችንን አይበትነውም፤ የለያዮን የመሰላቸው ህብረታችንን እናሳያቸዋለን የሚሉ እና ሌሎችም መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመርኃግብሩ ለፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በመዝጊያ መርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

(በሜሮን መስፍን)