በጅማ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

በጅማ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች የአሸባሪ ህወሓት ቡድንን በማውገዝ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ውሃ ሙሌት እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

የሀገራት ጣልቃ ገብነትም ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት ሰልፈኞች፣ በጅማ ስቴዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ እንደሚገኙ ከከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡