በጅማ ዞን በመብረቅ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ


ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) –
በጅማ ዞን ኖኖ ቤየም ወረዳ በመብረቅ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡
በወረዳው ኢልፈታ ቀበሌ ትናንት 10 ሰዓት አካባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በደረሰ የመብረቅ አደጋ ነው በእርሻ ስራ ላይ የነበሩ የአራት ሰዎች ህይወት ያለፈው፡፡
ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪም አንድ ሰንጋ መሞቱን ከወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡