በጅማ ዞን የልማት ጥያቄዎችን የሚመልሱ ተግባራት ተከናወኑ

መስከረም 27/2014 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ሸቤ ወረዳ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን የሚመልሱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) በጂማ ዞን ሸቤ ወረዳ በ10 ሚሊየን ብር ወጪ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጧል።

ትምህርት ቤቱን በአርባ ቀናት ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ የታቀደ ሲሆን፣ ወደ ስራ ሙሉ በሙሉ መገባቱም ተገልጿል።

የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢና የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አባ ዱላ ገመዳ ሀገር በመለወጥ ሂደት ውስጥ የተማረ የሰው ሃይል ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው  ብለዋል።

በተጨማሪም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ በ5 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተሰራ ከአንድ ሺሕ ብር በላይ ሠው የሚይዝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መርቀዋል።

ኦልማ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስንም ለትምህርት ቤቱ አስርክቧል፡፡