በጅቡቲ የበቃ #NoMore ዘመቻ ተካሄደ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የበቃ #NoMore ዘመቻን አካሄዱ።
በዚህም የውጭ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ የተዛባ መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል፤ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትም ተቃውመዋል።
በዘመቻው ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ዜጎች መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ተሳታፊዎቹ የአፍሪካ የሰላም ጉዞ (African Peace Walk) በሚል የ10 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ መርሃ ግብራቸውን ላይ ነው ዓለም ዐቀፉን ከኢትዮጵያና እውነት ጎን የመቆም ንቅናቄውን የተቀላቀሉት፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!