በጅዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺሕ 173 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

መጋቢት 23/2014 (ዋልታ) በጅዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺሕ 173 ዜጎች በሦስት በረራ በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመለሱ።

በሳውዲ አረቢያ ጅዳ በችግር ውስጥ የሚገኙ ህፃናትና ሴቶችን ጨምሮ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ  ቆይተው ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያንን መልሶ የማቋቋም ሥራ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በሚኒስቴሩ አስተባባሪነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ብሔራዊ ኮሚቴ ከስደት ተመላሾችን ለማቋቋም የተለያዩ ሥራዎች እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሱራፌል መንግሥቴ