በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ተወያየ

ሚያዝያ 3/2015 (ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

በውይይቱ ሚኒስትሩን ጨምሮ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት ውይይቱ ከፀደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ሲሆን ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና ከዓለም አቀፉ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይ ኤፍ ሲ) ፕሬዝዳንቶች፣ ዋና ዳይሬክተሮች እና ዳይሬክተሮች ጋር ተደርጓል።

በውይይቱም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ ምጣኔ ሀብት፣ ፋይናንስ እና አጋርነትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ልማት ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ መቅረቡ ተጠቁሟል።