በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በርበራ ገባ

ሰኔ 17/2013(ዋልታ) – የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ያካተተ ከፍተኛ ልዑክ ሶማሌላንድ በርበራ ገባ።

ልዑኩ በርበራ ሲደርስ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ልዑኩ ዛሬ የሚመረቀው የበርበራ ኮሪደር ወደብ ስነሥርዓት ላይ እንደሚሳተፍ ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡