«በጎ ሐሳብ ውጤት ባይኖረው እንኳን እንደ እንቁ ያበራል! »
የመፅሐፉ ርዕስ – ሰበዝ
ደራሲ – ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ
(በእየሩስ ወርቁ)
«…እሳቸው በደግነታቸው ለእኔ ያደረጉት እርዳታ የእኔን የምርምር ስራ የሚያጠፋና የሚያወድም እንደሆነ አልተረዱም ነበር፡፡ ተግባራቸው ለእኔ ጥፋት እንደሆነ ብረዳም ይህን ያገረጉት ደግሞ እኔን ለማገዝ ለእኔ ባላቸው ሐዘኔታ በመሆኑ የእሳቸው ደግነትና የምርምር ስራዬ ላይ የደረሰው ጥፋት አንድ ላይ አዕምሮዬ ውስጥ ገብቶ ጭንቅላቴን ናጠው፡፡… »
«…‹ በዓለም ላይ ትልልቅ ጥፋቶች የተፈፀሙት በጎ ሓሳብ ባላቸው ሰዎች ነው > የሚባለው ለዚህ ይሆን? በጎና ቅን ሃሳብ በጥበብና አርቆ በማየት ካልታሰበ መጨረሻው ጥፋት ሊሆን ይችላል፡፡ወደ ገሃነም የሚወስደው መንገድ በቅንነትና በየዋህነት የተገነባ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ እያልኩ በብዙ ተብሰከሰኩ፡፡…»
«… ደግነትና ሞራሊቲ የሚለካው በሚያመጣው ወይም በሚስከትለው ውጤት ሳይሆን ድርጊቱ በተፈጸመበት መንፈስ ብቻ ነው! በጎ ሐሳብ ውጤት ባይኖረው እናኳን እንደ እንቁ ያበራል¦
በጎ ሐሳብ በራሱ መልካም ነውና፡፡… »
ሰላም የተከበራችሁ የዚህ ገጽ ተከታታዮች
በዚህ ገጽ ስለ መፃሕፍት በስፋት የምንወያይበት ይሆናል፡፡ ወደ ፊት የተለያዩ ባለሙያዎችን በማወያየት ለናንተ ይጠቅማሉ ያልናቸውን ፍሬ ነገሮች ይዘን እንቀርባለን፡፡
እናንተም ለአንባቢያን ይጠቅማሉ የምትሏቸውን መፃሕፍት አስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልን፡፡
መልካም ንባብ