በጋሊ ኮማ ንፁሀን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ የሚያወገዝ ሰልፍ በሚሌ ከተማ ተካሄደ

ነሃሴ15/2013(ዋልታ) – የሚሌ ከተማ ነዋሪዎች በህወሀት የሽብር ቡድን ንፁሀን ላይ የደረሰውን የዘር ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰልፍ አካሄዱ።
በሰልፉ የሽብር ቡድኑ ህወሀት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያደረገ ያለው መፍጨርጨር እንደማይሳካ የአፋር ህዝብ በአንድነት የሽብር ቡድኑን ለማጥፋት እንደሚሰራ ተገልጿል።
በህፃናትና ሴቶች ላይ በደረሰው አሳዛኝ እልቂትም ህወሀት በዘር ማጥፋት ወንጀል ይጠየቅ የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ተሰምተዋል ኢቢሲ