በጋምቤላ ክልል የሕዝብ ውይይት መካሄድ ጀመረ

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) በጋምቤላ ክልል በአኙዋክ ብሔረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባዔ የሕዝብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የጋምቤላ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ ውይይቱ ብልፅግና ፓርቲ በጉባዔው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና አቋሞች ሕዝቡ እንዲገነዘባቸው እና ለተፈፃሚነታቸውም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አቅም ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
ብልፅግና ኅብረተሰቡን ከድህነት ለማውጣት እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አፈ ጉባኤዋ ኅብረተሰቡ ተማምኖበት የመረጠው እስከሆነ ድረስ ተያይዞ ለማደግ የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የአኙዋክ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኡቦንግ ኡጁሉ በበኩላቸው ፍትሃዊ እና አካታች የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ብልጽግና ትልቅ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡